Skip to content
Scan a barcode
Scan
Paperback Jehovah Nessi [Amharic] Book

ISBN: 108793740X

ISBN13: 9781087937403

Jehovah Nessi [Amharic]

ያህዌ ንሲ - በዓላማ መኖርሰዎች ለባንዲራዬ እሞታለሁ ሲሉ፣ ለጨርቁ ማለታቸው አይደለም፤ በዚያ ሰንደቅ ለተወከለው ታሪክ፣ እሴት፣ ባህል፣ ግዛት (territory)ና ዓላማ ማለታቸው ነው። በዚያ ባንዲራ ውስጥ ብዙ ነገር ያያሉ። ከራሳቸው የሚሰፋና የሚተልቅ ነገር ያያሉ። ሙሴ እንደ ሰንደቅ ዓላማ በትሩን ከፍ ካደረገ በኋላና አማሌቅን ካሸነፈ በኋላ እግዚአብሔር ዓላማዬ ነው ("ያህዌ ንሲ") የሚል መሠዊያ ሠራ። ለእግዚአብሔር ሕዝብ የድል መሠረት የሆነውን ነገር በዚህ መሠዊያ አሠመረበት። ከግብጽ የወጡ እስራኤላውያን ከራሳቸው የሚሰፋና የሚበልጥ ነገር ማየት ካልቻሉ፣ እግዚአብሔር ወዳሰበው ነገር ለመድረስና የሚፈልገውን ለመሆን ይቸገራሉ። ሰንደቅን የሚያይ ከራሱ የሰፋንና የተለቀን ነገር ማየት ይችላል። ያም ራሱን ሳይሆን "ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ" የሚያስችል አቋም ስለሚሰጠው በብዙ ነገር ከመጠላለፍ ይድናል (2ጢሞ 2፥4)።እስራኤላውያን ከግብጽ እንደ ወጡ ባጋጠማቸው በዚህ በመጀመሪያው ጦርነት "እግዚአብሔር ዓላማዬ ነው" የሚለው እንዲውለበለብላቸው ነው ያደረገው። እንዲሁ እኛም ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን እንደወጣን በውስጣችን ከፍ ብሎ ሊውለበለብ የሚገባው "እግዚአብሔር ዓላማዬ ነው" የሚለው ሰንደቅ ነው (ቆላ 1፥13-14)። በሕይወታችን ያሉ ሌሎች ሰንደቆች ሊወርዱና በዚህ ሰንደቅ ሊተኩ ይገባል። ይህ ሰንደቅ ከፍ ብሎ ካልተውለበለበና ካልታየን ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን ብንወጣም፣ ነገር ግን በጉዞአችን ውስጥ ባሉ የተለያዩ ነገሮች ተሰነካክለን ወደታሰበልን ግብ ከመድረስ እንገታለን።


Recommended

Format: Paperback

Condition: New

$12.30
50 Available
Ships within 2-3 days

Customer Reviews

0 rating
Copyright © 2025 Thriftbooks.com Terms of Use | Privacy Policy | Do Not Sell/Share My Personal Information | Cookie Policy | Cookie Preferences | Accessibility Statement
ThriftBooks ® and the ThriftBooks ® logo are registered trademarks of Thrift Books Global, LLC
GoDaddy Verified and Secured